በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የተወገዱት የጋቦኑ ፕሬዝዳንት የእርዳታ ጥሪ አስተላለፉ

1 Yr Ago 1380
በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የተወገዱት የጋቦኑ ፕሬዝዳንት የእርዳታ ጥሪ አስተላለፉ

በወታደራዊ አመራሮች መፈንቅለ መንግስት ተፈጽሞባቸው በቁም እስር ላይ የሚገኙት የጋቦኑ ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ የእርዳታ ጥሪ አቅርበዋል፡፡  

ፕሬዝዳንቱ ከመኖሪያ ቤታቸው ቀርጸው ባስተላለፉት አጭር የቪዲዮ መልዕክት አለም አቀፉ ማህበረሰብ መፈንቅለ መንግስቱን በመቃወም ድምጹን እንዲያሰማ ጠይቀዋል፡፡

“ምን እየተከናወነ እንዳለ ለመረዳት አልቻልኩም” ያሉት ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎ ባለቤታቸው እና ልጃቸው ከእርሳቸው ተለይተው በተለያየ ስፍራ እንዲቀመጡ መደረጉ እንዳሳሰባቸውም ተናግረዋል፡፡

በጋቦን ወታደራዊ አመራሮች ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎን በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን ማንሳታቸውን በብሔራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ አስታውቀዋል፡፡

ወታደሮቹ በሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ ተካሂዶ በሁለት ሶስተኛ ድምጽ ፕሬዝዳንቱ አሸንፈዋል የተባለበትን የምርጫ ውጤት መሻራቸውንም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top