አሜሪካ ሰሜን ኮሪያን አስጠነቀቀች

3 Mons Ago
አሜሪካ ሰሜን ኮሪያን አስጠነቀቀች

ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ የጦር መሳሪያዎችን እየሸጠች ነው በሚል አሜሪካ ሀገሪቱን ማስጠንቀቋ ተሰምቷል፡፡

ፒዮንጊያንግ ለሩሲያ የጦር መሳሪያዎችን በመሸጥ ላይ መሆኗ የተነገረው በአሜሪካ እና በሰሜን ኮሪያ መካከል ያለው ውጥረት ጫፍ በደረሰበት ወቅት ነው፡፡

አሜሪካ በሩሲያ እና በሰሜን ኮሪያ መካከል ያለው ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ንግድ  እንዳሳሰባት የዋይት ሃውስ የብሔራዊ ደህንነት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ ተናግረዋል፡፡

ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ የጦር መሳሪያዎችን ለማቅረብ አሊያም ለመሸጥ እያደረገችው ያለውን ድርድርን እንድታቆምም ቃል አቀባዩ ጠይቀዋል፡፡

አሜሪካ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገችው ባለው ጦርት ለሞስኮ ድጋፍ የሚያደርጉ ሀገራትን ስታስጠነቅቅ መቆየቷን አል ጃዚራ ዘግቧል፡፡  

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top