የኢትዮጵያ መንግሥት በከተማ አረንጓዴ መሠረተ ልማት ዝርጋታ ላይ በስፋት እየሠራ ነው፦ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ

1 Yr Ago 550
የኢትዮጵያ መንግሥት በከተማ አረንጓዴ መሠረተ ልማት ዝርጋታ ላይ በስፋት እየሠራ ነው፦ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ

በከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ የተመራ የልዑካን ቡድን በፓሪስ ከተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

ልዕካን ቡድኑ ከፓሪስ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ዳይሬክተር፣ የከተሞች የአየር ንብረት ኃላፊ እና የሥነ-ምኅዳር እና የአየር ንብረት ለውጥ ዲፓርትመንት ኃላፊ ጋር ስለ ከተሞች የመበደር ብቃት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ ከተሞችን ስለመገንባት ውይይት አድርጓል።

ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ መንግሥት በከተማ የአረንጓዴ መሠረተ ልማት ዝርጋታ ላይ በስፋት እየሠራ እንደሆነ አብራርተዋል።

በተያያዘም የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የከተማ ተቋማዊ እና የመሠረተ ልማት ዝርጋታ መርሐ ግብሮችን በመንደፍ እንዲሁም በከተሞች የሚስተዋለውን ድህነት ለመቅረፍ የሥራ ዕድል በመፍጠር እና የከተማውን ማኅበረሰብ የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ በስፋት እየሠራ እንደሆነ ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከተለያዩ ሀገር በቀል እና ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አከላት እና ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሀገሪቱ ያሉትን ከተሞች የገንዘብ እና ተቋማዊ አቅም ለማሳደግ ያለመ በርካታ የከተማ አቀፍ ፕሮግራሞችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ነው ሚኒስትሯ ያነሱት።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top