የኢትዮጵያ እና የፓኪስታን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በሁሉም መስክ ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል- አምባሳደር ጀማል በከር

1 Yr Ago 382
የኢትዮጵያ እና የፓኪስታን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በሁሉም መስክ ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል- አምባሳደር ጀማል በከር

የኢትዮጵያ እና የፓኪስታን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በሁሉም መስክ ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሩን በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር ገለጹ።

በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሥራ የጀመረበትን አንደኛ ዓመት በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብሯል።

የሁለቱን አገሮች የዲፕሎማሲ ግንኙነት እና በትብብር እያከናወኗቸው ያሉ ተግባራትን በተመለከተ ኢዜአ በፓኪስታን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ጀማል በከርን አነጋግሯል።

አምባሳደሩ በማብራሪያቸው የሁለቱ አገራት ግንኙነት በተለይም ከለውጡ ወዲህ በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ እና በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ግንኙነት ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።

የሁለቱን አገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር የሚያስችሉ የትብብር ማዕቀፎች በመተግበር ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ላይ ይደረጉ የነበሩ ያልተገቡ የውጭ ጫናዎችን በመቃወም ፓኪስታን ከኢትዮጵያ ጎን መሆኗን በተግባር ማሳየቷንም አምባሳደሩ አስታውሰዋል።

በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ በተለይም በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝም እና ሌሎች ዘርፎች ትብብራቸው እያደገ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፓኪስታን ካራቺ በራራ መጀመሩም ለሁለቱ አገሮች የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መጠናከር መልካም አጋጣሚ የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል። 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top