Ethiopia has told me that Ethiopia will one day divide itself into a nation-wide divide in Ethiopia - BBC News Journal

5 Yrs Ago
Ethiopia has told me that Ethiopia will one day divide itself into a nation-wide divide in Ethiopia - BBC News Journal

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብሔር የመከፋፈል አዝማሚያ የሚታይባትን ኢትዮጵያን አንድ እንደሚያደርጓት መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

የቢቢሲ አፍሪካ ኤዲተር ፈርጋል ኪን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ ጅማ ሄደው በነበረበት ወቅት እዚያ አግኝቷቸው በብሔር የመከፋፈል አዝማሚያ የሚታይባትን አገር አንድ የሚያደርጋት ሰው እሳቸው እንደሆኑ ዶ/ር ዐቢይን ጠይቋቸው ነበር፡፡

ዶ/ር ዐቢይም በርግጥም አገሪቱን አንድ እንደሚያደርጓትና ለዚህ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ እንዳይገባው ነግረውታል።

በወቅቱ በሁሉም የዕድሜ ክልል የሚገኙ በርካታ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች በኤርፖርት ተገኝተው ጠቅላይ ሚኒስትሩን በደማቅ ሁኔታ እንደተቀበሏቸው የዓይን እማኙ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ተናግሯል።

በኤርፖርት ተሰብስበው ከነበሩት የከተማዋ ነዋሪዎች ውስጥ በዕድሜ ገፋ ያለ አንድ ሰው ወደ ጋዜጠኛው ቀርቦ ነዋሪዎቹ በጣም ደስተኞች እንደሆኑና ይህን ቀን ለማየት ብዙ እንደጠበቁ ነግሮታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ተማሪዎች ምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ ተማሪዎች ሃሳብ እንጂ ጥይት እንዳይጠቀሙ መክረዋቸዋል ይላል ጋዜጠኛው። ለዚህ ደግሞ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት አገግማ በጣም ትልቅ ኢኮኖሚ የገነባችውን ጃፓንን ምሳሌ እንዲያደርጉም ነግረዋቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚስትሩ እያደገ የመጣውን የብሔር ግጭት እንዲቃወሙ በጅማ ለተመራቂዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጋዜጠኛ ፈርጋል ኪን ወደ ትግራይም ተጉዞ ነበር። በትግራይ በአብዛኛው የሚወራው ስለ ህወሓት ከስልጣን መገለል እንደሆነ ጋዜጠኛው ገልጿል።

የቀድሞው የኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ባለፈው ጊዜ ለተፈጠረው ስህተት የትግራይ መሪዎች ብቻ ተጠያቂ እንደሆኑ ተደርጎ እየታሰበ መሆኑን ለጋዜጠኛው ነግረውታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ በትግራይም ድጋፍ እንዳላቸው ጋዜጠኛ ፈርጋል ኪን ካነጋገራቸው ሰዎች ተረድቷል።

በአነስተኛ ማሳ ግብርና የምትተዳደረው ኤልሳ ተስፋዬ በኤርትራ አዋሳኝ የትግራይ አካባቢ የምትኖር ሲሆን በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ሁለት ወንድሞቿን አጥታለች። ዶ/ር አብይ ለእርሷ ሰላምን ያመጣ ሰው ስለሆነ እንደምታመሰግነው ተናግራለች።

የብሔር ክፍፍሉ ግን እንደሚያሰጋት የጠቆመችው ኤልሳ፣ ነገሮች በዚሁ ከቀጠሉ የኢንጂነሪንግ ተማሪ ልጇ ወደሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ሄዶ ስራ ማግኘት አይችልም ብላ ትሰጋለች።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top