ኢትዮ-ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት የደንበኞቹን ቁጥር 78 ሚሊየን ለማድረስ ማቀዱን ገለጸ

4 Mons Ago
ኢትዮ-ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት የደንበኞቹን ቁጥር 78 ሚሊየን ለማድረስ ማቀዱን ገለጸ

ኩባንያው በሞባይል 74.74 ሚሊዮን፣ የሞባይል ዳታ እና ኢንተርኔት 41.17 ሚሊዮን፣ የፊክስድ ብሮድባንድ 842.68 ሺህ ተጠቃሚዎችን በማድረስ አጠቃላይ የቴሌኮም ስርፀት መጠንን 71 በመቶ ለማድረስ ማቀዱን ገልጿል።

የቴሌብር ደንበኞች ቁጥርንም በ28.5 በመቶ በመጨመር 44.1 ሚሊየን ለማድረስ ማቀዱን ነው የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የገለጹት።

ኢትዮ-ቴሌኮም በአገልግሎቱ 90.5 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት ማቀዱንም ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል።

ኩባንያው በውድድር ገበያው ደንበኞችን ለማርካት እና ተደራሽነቱን በማስፋት ቀልጣፋ እና አስተማማኝ አገልግሎት እንሰጣለን ሲሉም ተናግረዋል።

በቅድስት ማሞ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top