እውቅናውን የሰጠው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲሆን በዚህም ለአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላም እና ደኅንነት ኮሚሽን እንዲሁም ቡድን የእውቅና መርሐ-ግብር ተካሂዷል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በቅርቡ አፍሪካ ኅብረት ላደረገው አስተዋጽኦ በአጠቃላይ እና ኢትዮጵያ የሰጠችውን እውቅና አስታውሰዋል።
በአፍሪካ ኅብረት ለሚመራው የሰላም ሂደት እና የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ስኬት ለፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሰላም እና ደኅንነት አመራር እና ቡድኑ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የእውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷል።
በስምምነቱ ወቅት የተደረሰው ስምምነት አፈጻጻም ቀጣይነት ያለው ዕድገት እያስመዘገበ መሆኑን እና ለተሟላ እና ወቅታዊ ትግበራም መንግሥት ቁርጠኛ ነው ብለዋል።
በአፍሪካ ኅብረት ድጋፍ እና አስተዋጽኦ ቀሪ ሥራዎች ተግባራዊ እንደሚሆኑም አቶ ደመቀ ጠቁመዋል።
የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሰላም እና ፀጥታ ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ በበኩላቸው፣ ለፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ስኬት እውቅና በማግኘታቸው አመስግነዋል።
በአንዳንድ የአፍሪካ አገራት ያሉ ግጭቶች ከኢትዮጵያ ልምድ በመውሰድ ወደ መፍትሔ መምጣት እንደሚቻል መማር እንደሚገባ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።