በደቡብ ክልል ሁለተኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በጌዲኦ ዞን ተጀምሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ወናጎ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

አካባቢው በቡና፣ አቮካዶ፣ ማንጎና ሌሎች የፍራፍሬ ተክሎች በስፋት የሚታወቅ ሲሆን፤ በዘንድሮው አረንጓዴ ዐሻራ በጥምር ደን ልማት ላይ ትኩረት ይደረጋል ተብሏል።
በክልሉ በተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው አሻራቸውን አኑረዋል።


በሮዛ መኮንን