የቀድሞው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰለሞን አረዳ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የግልግል ፍርድ ቤት የግማሽ ጊዜ ዳኛ በመሆን ቃለ መሐላ ፈፅመዋል።
አቶ ሰለሞን እ.ኤ.አ ኖቨምበር 15 ቀን 2022 በኒው ዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ የፍርድ ቤቱ የግማሽ ጊዜ ዳኛ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።
በዚሁ መሠረት አቶ ሰለሞን አዲሱን ሥራቸውን ከመጀመራቸው በፊት ባሳለፍነው ሳምንት በኒው ዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት በሕጉ መሠረት የቃለ መሐላ ሥነ-ሥርዓት ፈጽመዋል።
ቃለ መሐላውን ያስፈጸሙት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ናቸው።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የግልግል ፍርድ ቤት በድርጅቱ ውስጥ የሚነሡ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ዳኝነት የሚሰጥ ትልቅ የዳኝነት አካል ነው።