የመዝናኛውን ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር ኢቢሲ ልዩ ሥራ እና አሰራር ይዞ መምጣቱ ተገለጸ

2 Yrs Ago 518
የመዝናኛውን ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር ኢቢሲ ልዩ ሥራ እና አሰራር ይዞ መምጣቱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከተለያዩ አንጋፋና ወጣት የሀገራችን የጥበብ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ያዘጋጃቸውን የቴሌቪዥን ድራማዎች ትናንት በሸራተን አዲስ ሆቴል በደማቅ ሥነ ስርዓት አስመርቋል።

ድራማዎቹ በተለያየ ዘውግ የተሰሩ ሲሆን ከቀናት በኋላ ማለትም ከሰኔ 18 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በየሳምንቱ ለህዝብ መቅረብ ይጀምራሉ።

የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍሰሃ ይታገሱ በምርቃት ሥነስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ኮርፖሬሽኑ በአሁኑ ወቅት የአድማጭ ተመልካች ፍላጎትን ለማርካት እና የተጣለበትን ማህበራዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ከፍተኛና ሁለንተናዊ ተቋማዊ የሪፎርም ስራዎች በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

አድማጭ ተመልካቹ የተሻለ አማራጭ እና ተመራጭ የሚዲያ ይዘት እንዲያገኝ ተቋሙ በተለያዩ ቻናሎቹ ከፍተኛ የለውጥ ሥራዎች እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በመዝናኛው ዘርፍ ቀዳሚና ግንባር ቀደም የሀገሪቱ ሚዲያ ሆኖ እንዲቀጥል አዳዲስ የፕሮግራም እና የድራማ ይዘቶችን በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በውስጥ አቅም ከሚሰሩ በርካታ ፕሮግራሞች በተጨማሪ በሀገራችን ያሉ ዕንቁ የጥበብ ባለሙያዎችን በማስተባበርና በማሳተፍ የመዝናኛ ኢንዱስትሪውን የላቀ ደረጃ በማድረስ በሀገሪቱ ሁለንተናዊ ለውጥ ውስጥ ኢቢሲ ልዩ ሚና እንደሚወጣ አቶ ፍሰሃ ገልጸዋል።

የኢቲቪ መዝናኛ ቻናል ማኔጂንግ ኤዲተር አቶ ዘካርያስ ብርሃኑ ተመርቀው በየሳምንቱ መታየት በሚጀምሩት ስድስት ድራማዎች ከፍተኛ ልምድና ዝና ያላቸው የሀገራችን የጥበብ ባለሙያዎች እንደተሳተፉባቸው ገልጸው፤ በይዘትና አቀራረብ ተመልካች እንዲወዳቸውና መርጦ እንዲመለከታቸው ከፍተኛ ጥንቃቄና ጊዜ ተወስዶ ዝግጅት የተደረገባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ትናንት የደመቀ የመክፈቻና የማስመረቂያ ሥነስርዓት የተካሄደላቸው የኢቢሲ አዳዲስ ድራማዎች እና ሳምንታዊ የመተላለፊያ ቀንና ሰዓታቸው የሚከተለው ነው፥

📌 "ግራ ቀኝ"... እሁድ ቀን 8 ሰዓት በዜና ቻናል እንዲሁም ማታ 2 ሰዓት በመዝናኛ ቻናል

📌 "በመሐል"...ሰኞ ማታ 2:20 በመዝናኛ ቻናል

📌 "እቴጌ"...በሳምንት ሁለት ጊዜ ረቡዕ እና አርብ ማታ 2:20 በመዝናኛ ቻናል

📌 "ደርዳሬ"(ኮሜድያን ደረጄ ሐይሌ)...እሁድ ቀን 9:30 በመዝናኛ ቻናል

📌 "ሲምቦ"...አርብ ማታ 3:20 በአፋን ኦሮሞ ቻናል

📌 "ሒርኮ"...እሁድ ከሰዓት በኋላ በአፋን ኦሮሞ ቻናል በዳንጋ የመዝናኛ ፕሮግራም ይቀርባሉ።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top