የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከሩስያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ መከሩ

6 Mons Ago
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከሩስያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ መከሩ

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በዩክሬን ሩስያ ግጭት ዙሪያ አፍሪካ ለሰላም ስለምታደርገው ጥረት ከሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ መምከራቸው ተገለጸ።

ከክሬምሊን እንደተሰማው መረጃ፣ ፕሬዚዳንት ፑቲን በቅርቡ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችን የያዘ ልዑክ ተቀብለው ያነጋግራሉ።

የሁለቱ ሀገራት ፕሬዚዳንቶች ውይይት ከዚህም ባለፈ በመጪው ሐምሌ በሩስያ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ስለሚካሄደው 2ኛው የሩስያ አፍሪካ ጉባኤ እና በነሐሴ ወር በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ስለሚደረገው የብሪክስ ጉባኤ መክረዋል።

ነገር ግን ፑቲን በብሪክስ ጉባኤ ስለመገኘታቸው የተባለ ነገር የለም።

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ባለፈው ማክሰኞ እንዳስታወቀው፣ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በዩክሬን እና ሩስያ መካከል የተኩስ አቁም በሚደረግበት እና በቀጠናው ሰላም በሚሰፍንበት አግባብ ዙሪያ ከሌሎች 5 የአፍሪካ ሀገራት ጋር መክረዋል።

በቀጣይም በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ ከሁለቱ ሀገራት መሪዎች ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል የዘገበው የደቡብ አፍሪካው ኤስኤቢሲ ነው።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top