የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድ ከ12 ዓመታት በኋላ የአረብ ሊግ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ሳውዲ አረቢያ ገቡ

10 Mons Ago
የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድ ከ12 ዓመታት በኋላ የአረብ ሊግ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ሳውዲ አረቢያ ገቡ

የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድ ከ12 ዓመታት ቆይታ በኋላ የአረብ ሊግ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ሳውዲ አረቢያ መግባታቸው ተገለጸ።

ከግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ከቀጠፈው ጦርነት በኋላ ሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳውዲ አረቢያ በምታስተናግደው የአረብ ሊግ የመሪዎች ጉባኤ ላይ እንደምትሳተፍ ተገልጿል።

ሶሪያ ከዚህ ቀደም ተቀዋሚ ኃይሎችን ሲደግፉ የነበሩ የአረብ ሀገሮች የአላሳድን በስልጣን የመቆየት ጉዳይ በመቀበላቸው ምክንያት ወደ ሊጉ ለመመለስ በቅርብ ወራት መወሰኗን ዘገባው ጠቅሷል።

በቅርቡ በቱርክ እና ሶሪያ በተከሰተው ርዕደ መሬት ባላንጣ የነበሩ አካላት የነፍስ አድን እርዳታ ለማቅረብ በጋራ መረባረባቸው አንዱ መነሻ እንደሆነ ተጠቅሷል።

ፕሬዝዳንት አሳድ በጉባኤው ለመሳተፍ ጅዳ የገቡ ሲሆን የአዘጋጅ ሀገር የሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጨምሮ ሌሎች አባል ሀገራት በሶሪያ እንደገና መመለስ ደስታቸውን ገልጸዋል።

ከአባል ሀገራቱ ኳታር የአሳድን መመለስ እንደማትደግፍ እና ከሊጉ ሀገራት ስምምነት ውጭ እንደሆነ ገልፃለች።

ሶሪያ አሁንም ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ እንዳለባት የጠቆመው የቢቢስ ዘገባ፣ ከ15 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብሏል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top