የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መስፈን እያከናወነች ያለውን ተግባራት አጠናክራ ትቀጥላለች፦ ቅዱስ ሲኖዶሱ

11 Mons Ago
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መስፈን እያከናወነች ያለውን ተግባራት አጠናክራ ትቀጥላለች፦ ቅዱስ ሲኖዶሱ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መስፈን እና ለምዕመናን ደኅንነት እያከናወነች ያለውን ተግባራት አጠናክራ እንደምትቀጥል የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ገለጸ።

ዓመታዊው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጉባዔው በተጀመረበት ወቅት እንደገለጹት፣ ቤተክርስቲያኗ ከመንፈሳዊ ተግባራት ጎን ለጎን የሰላም፣ የዕርቅ እና ሌሎች ዕሴቶችን ለምዕመኑ የማስተማር ሥራዎች እያከናወነች ትገኛለች።

ይህንን ተግባሯን በማጠናከር አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን የቤተክርስቲያኗ አባቶች ተግተው ሊሠሩ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

በአንዳንድ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን በውይይት እና መግባባት መፍታት ይገባልም ብለዋል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ በቤተክርስቲያኗ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ እንደሚወያይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጠቁመዋል።

በይድነቃቸው ሰማው


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top