በኮትዲቯር አዘጋጅነት በሚካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዋልያዎቹ ከማላዊ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ በሞዛምቢክ እንደሚካሂድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

6 Mons Ago

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ የምድቡ አምስተኛ መርሐ-ግብር ሲሆን፣ ጨዋታው ሰኔ 13 ቀን 2015 ይከናወናል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት በሚገኙ ስታዲየሞች ላይ ጨዋታው እንዲከናወን ያደረገው ጥረት ባለመሳካቱ ጨዋታውን ለማከናወን ሞዛምቢክን ምርጫው ማድረጉን ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ማሳወቁን ገልጿል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያው በምድብ አራት ከግብጽ፣ ጊኒ እና ማላዊ ጋር ተመድባ ጨዋታዋን በማድረግ ላይ ትገኛለች።
ዋልያዎቹ ቀደም ሲል በሞሮኮ ባከናወኑት 3ኛ እና 4ኛ የምድብ ጨዋታዎች በጊኒ አቻው በደርሶ መልስ መሸነፋቸውን ተከትሎ በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ይገኛሉ።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top