በግንቦት ወር በደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ የዝናብ ስርጭት ይኖራል፦ ኢጋድ

1 Yr Ago
በግንቦት ወር በደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ የዝናብ ስርጭት ይኖራል፦ ኢጋድ
በግንቦት ወር በደቡብ ምሥራቅ የኢትዮጵያ አካባቢዎች መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ የዝናብ ስርጭት አንደሚኖር የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) አስታወቀ።
ኢጋድ የአፍሪካ ቀንድ ቀጠናን የቀጣይ ወራት የአየር ሁኔታ በተመለከተ በድረ-ገጹ ባሰፈረው ትንበያ፣ በመጪው ግንቦት ወር በኢትዮጵያ ደቡባዊ ምሥራቅ አከባቢ፣ በሶማሊያ እና ተንዛኒያ በቂ እና ከበቂ በላይ ዝናብ እንደሚያገኙ አስተውቋል።
አጠቃላይ የቀጠናው ሰሜናዊ እና መካከለኛው አካባቢዎች ደረቃማ እና ከመደበኛ ያነሰ ዝናብ እንደሚጠበቅም ገልጿል።
የሙቀት መጠንን በተመለከተ ደግሞ አብዛኛው የኢትዮጵያ አካባቢዎች አማካይ ሙቀት እንደሚኖራቸው እና በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ አዋሳኝ አካባቢዎች እንዲሁም በሰሜን ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከአማካይ ያነሰ ሙቀት እንደሚኖራቸው ኢጋድ በትንበያው አስታውቋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top