"የኢትዮጵያ ረቂቅ ሙዚቃዎች እናት" እማሆይ ጽጌማርያም ገብሩ በ100 ዓመታቸው አረፉ

1 Yr Ago 341
"የኢትዮጵያ ረቂቅ ሙዚቃዎች እናት" እማሆይ ጽጌማርያም ገብሩ በ100 ዓመታቸው አረፉ
"የኢትዮጵያ ረቂቅ ሙዚቃዎች እናት" እማሆይ ጽጌማርያም ገብሩ በተወለዱ በ100 ዓመታቸው አርፈዋል።
በፒያኖ የሙዚቃ ሥራዎቻቸው “የፒያኖዋ እመቤት” የሚል ስያሜን ማግኘት የቻሉት የቀድሞዋ የውብዳር ገብሩ፣ የአሁኗ እማሆይ ጽጌማርያም ገብሩ እ.ኢ.አ ታኅሣሥ 4 ቀን በ1915 ዓ.ም ከአባታቸው ከከንቲባ ገብሩ ደስታ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ካሣዬ የለምቱ ተወለዱ።
እማሆይ ጽጌማርያም ትምህርታቸውን ስዊትዘርላንድ ውስጥ የተከታተሉ ሲሆን፣ የሙዚቃ መሣሪያዎቹን መጫወት የተማሩትም እዚያው ነበር።
በአስራዎቹ ዕድሜያቸው መጨረሻ ላይ ወደ አገራቸው ሲመለሱም ወደ መንፈሳዊ ሕይወት በማዘንበል በ21 ዓመታቸው ምንኩስናን በመቀበል ዘመናቸውን ኖረዋል።
ከ30 ዓመታት በፊት ደግሞ ወደ እስራኤል በመሄድ ኢሩሳሌም ውስጥ በገዳማት ውስጥ ሲኖሩ ቆይተው በ100 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ ከ150 በላይ የረቂቅ ሙዚቃ ድርሰቶችን የጻፉ፤ ሦስት አልበሞችን በሲዲ እና በሸክላ ላይ ያሳተሙ ናቸው።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top