የተለያዩ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች በሀገራዊ እና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያዩ ነው

8 Mons Ago
የተለያዩ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች በሀገራዊ እና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያዩ ነው

የደቡብ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ እና ሐረሪ ክልል ከፍተኛ አመራሮች "ድሎችን የማጽናት እና ፈተናዎችን የመሻገር ወቅታዊ እና ታሪካዊ አመራሮች ተልዕኮ" በሚል ርዕስ በሀገራዊ እና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ።

በደቡብ ክልል ሐዋሳ እየተካሄደ በሚገኘው የውይይት መድረክ ከክልል፣ ከዞን፣ ከልዩ ወረዳ፣ ከወረዳ እና ከከተሞች የተውጣጡ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሳተፊ ናቸው።

የብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ በመድረኩ እንዳሉት፤ ብቃት ያለው አመራር በመፍጠር ረገድ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እየተካሄደ በሚገኘው የውይይት መድረክ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ተወካይ አቶ ባበክር ኻሊፋ ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።