55ኛው የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚ ልማት እና ፕላን ሚኒስትሮች መደበኛ ስብስባ ተጀመረ

1 Yr Ago
55ኛው የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚ ልማት እና ፕላን ሚኒስትሮች መደበኛ ስብስባ ተጀመረ
55ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚ ልማት እና ፕላን ሚኒስትሮች መደበኛ ስብስባ ዛሬ በሚኒስትሮች ደረጃ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
ስብሰባው “የአፍሪካ መልሶ ማገገምና ለውጥን በማፋጠን ፣ ኢ-ፍትሐዊነት እና ተጋላጭነትን መቀነስ” በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው።
በስብሰባው መክፈቻ ላይ የኮሚሽኑ አባል አገራት የፋይናንስ፣ እቅድ እና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሮች እና ተወካዮች ፣ የተመድ ተቋማት ኃላፊዎች፣ የልማት አጋሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
መደበኛ ስብሰባው ለሶስት ቀናት በባለሙያዎች ደረጃ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል።
ባለሙያዎቹ በአፍሪካ ያለውን ድህነት እና ኢ-ፍትሐዊነት እንዲሁም ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
ቀጣናዊ ትስስር ላይ ያሉ ለውጦች ጨምሮ ሌሎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይም መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ሚኒስትሮቹ የኮሚሽኑ ባለሙያዎች ተወያይተው ባቀረቧቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሚኒስትሮች ስብሰባው ለሁለት ቀናት የሚቆይ መሆኑ ተመላክቷል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top