የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ "ዘካት" የተሰኘ ልዩ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት ጀመረ

1 Yr Ago 17295
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ "ዘካት" የተሰኘ ልዩ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት ጀመረ

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በሚሰጠው የወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት "ዘካት" የተሰኘ ልዩ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት መጀመሩን አስታውቋል።

ባንኩ 'አልሁዳ' በሚል የወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ወዲህ የተለያዩ ከወለድ ነፃ አገልግሎቶችን እያደረሰ ይገኛል።

"ዘካት" የተሰኘው የቁጠባ ሒሳብም ደንበኞች ካላቸው ሀብት የተወሰነውን በጥሬ ገንዘብ፣ በዓይነት እና በሌሎች አማራጮች 'ዘካ'ን /ምፅዋትን/ ለመክፈል የሚያስችል ነው።

ይኸው የቁጠባ ሒሳብ በሁለት ዓይነት እንደሚቀርብ የተገለጸ ሲሆን አንደኛው ደንበኞች ከሀብታቸው ላይ ዘካት ማውጣት የሚጠበቅባቸውን በመቆጠብ ክፍያ እንዲፈፅሙ የሚያስችል ሲሆን ሌላኛው ባንኩ በሚከፍተው የዘካት ሒሳብ ላይ ደንበኞች ክፍያን በማሰባሰብ በደንበኛው ፍላጎት ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች የሚተላለፍ መሆኑ ተገልጿል።

"ዘካት" የቁጠባ ሒሳብ ማኅበራዊ እሴትን በማጠናከር ረገድ የሚኖረው ሚና የጎላ መሆኑም ነው የተገለጸው።

በሙሐመድ አልቃድር


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top