የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 100 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

1 Yr Ago 558
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 100 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 100 ሺህ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
አስተዳደሩ የህዝቡን የቤት ጥያቄ ለመመለስ በመንግስት እና በግል አጋርነት የሚሰሩ የመጀመሪያ ዙር 100 ሺህ ቤቶችን ግንባታ ፕሮጀክት ለማስጀመር የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት አካሂዷል።
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት፣ በከተማችን ያለውን የቤት አቅርቦት እጥረት መንግስት ለብቻው የሚፈታው ባለመሆኑ፣ ልበ ቀና ባለሃብቶችን በማሳተፍ መካከለኛ ገቢ ያላቸው የከተማችን ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመረው ይህ የቤት ግንባታ ፕሮጀክት ህዝባችንን ለማገልገል የገባነውን ቃል በማክበር የህዝቡን ችግር ለሚቀርፉ ስራዎች ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።
ለመጀመሪያ ዙር ግንባታም በመንግስት 350 ሄክታር መሬት መዘጋጀቱ ነው የተገለጸው።
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ 68 የሀገር ውስጥና የውጭ አልሚ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top