መከላከያ ሚኒስቴር በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 220 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

1 Yr Ago
መከላከያ ሚኒስቴር በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 220 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
የመከላከያ ሚኒስቴር በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 220 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።
የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉውጂ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ ሰራዊቱ የህዝብ ልጅ በመሆኑ የአገርና ህዝብን ሰላምንና ደህንነት ከማስጠበቅ በተጨማሪ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል፡፡
ሰራዊቱ በቀጣይም ለዜጎች ያለውን አለኝታነት በተግባር እያረጋገጠ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በዚህም ሚኒስቴሩ በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች 100 ሚሊዮን ብር፣ ለሱማሌ 50 ሚሊዮን ብር፣ ለደቡብ ክልል 40 ሚሊዮን እንዲሁም በአማራ ክልል ዋግ ኸምራ ዞን 30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን የመከላከያ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል ፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top