21 ቢሊየን ብር ድጎማ በማድረግ የአፈር ማዳበርያ ወደ ሃገር ውስጥ እያስገባን ነው - ግብርና ሚኒስቴር

1 Yr Ago 376
21 ቢሊየን ብር ድጎማ በማድረግ የአፈር ማዳበርያ ወደ ሃገር ውስጥ እያስገባን ነው - ግብርና ሚኒስቴር
ለ2015/16 የመኸር ወቅት የማዳበሪያ ግዥ ላይ 21 ቢሊየን ብር ድጎማ መደረጉን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለተያዘው የመኸር ወቅት የማዳበሪያ ግብዓትን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
መግለጫውን የሰጡት የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ፣ መንግስት ያለውን የትራንስፖርትና አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የማዳበሪያ ግብአት ግዥ ላይ 21 ቢሊየን ብር ድጎማ መደረጉን ተናግረዋል።
የግብርና ሚኒስቴር በአፈር ማዳበሪያ ዙሪያ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው በ1 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ላይ 1ሺህ566 ብር ድጎማ ተደርጓል።
የግብርና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በአሁኑ ሰዓት 12.8 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበርያ ተገዝቶ ወደ ሃገር ዉስጥ እየገባ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በዘንድሮው የመኽር የበልግ እና የመስኖ ልማት ላይም 15 ሚሊየን ኩንታል ያህል ማዳበሪያ ጥቅም ላይ ይውላል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል።
1.5 ሚሊየን ሊትር አግሮ ኬሚካሎችም በመኽር እና በልግ ለሚለሙ ሰብሎች እንደሚያስፈልጉ የተገለጸ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 970ሺህ ሊትር የሚሆነው ተደራሽ ተድርጓል ተብሏል።
በመለሰ አምዴ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top