ሁዋዌ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በስፔን ባርሴሎኖ በተካሄደው የሞባይል ቴክኖሎጂ ኮንግረስ ላይ አዳዲስ ፈጠራዎችን ይፋ አደረገ

9 Mons Ago
ሁዋዌ የቴክኖሎጂ ኩባንያ  በስፔን ባርሴሎኖ በተካሄደው የሞባይል ቴክኖሎጂ ኮንግረስ  ላይ አዳዲስ ፈጠራዎችን ይፋ አደረገ

ከየካቲት 20-23፣2015 ድረስ  በስፔን ባርሴሎና  በተካሄደው የሞባይል ቴክኖሎጂ ኮንግረስ ላይ  በሞባይል ትስስር ኢንዱስትሪው  በዲጂታል ዓለም ውስጥ ለውጥ የሚያመጡ ስራዎች ቀርበውበታል።

በኮንግረሱ ላይ ተሳታፊ የነበረው  ሁዋዌ ኩባንያ በኢንዱስትሪው  ውስጥ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ አዳዲስ  ፈጠራዎችን ይዞ መቅረቡንም አስታውቋል።

በተለይም በክላውድ  ቴክኖሎጂ የመረጃ  መሰረተ ልማትን ለመገንባት የሚያስችል አዲስ የመረጃ ቋት ፣የዲጂታል ዓለሙ የክላውድ ቴክኖሎጂ አዲስ ገፀ በረከት ፣የዲጂታል አስታውሎት አገልግሎት እና ለዘመነው ዓለም የሚውል የመረጃ ቋት  በመድረኩ ላይ ይፋ  ከሆኑ የቴኬኖሎጂው  ዘርፍ ግኝት ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው።

ኩባንያው በ”ምርጥ የሞባይል ኔትዎርክ መሰረተ ልማት”  እና በ”ምርጥ የሞባይል ቴክኖሎጂ ፈጠራ” በመድረኩ ላይ ተሸላሚ እንደነበርም ሁዋዌ ለኢቢሲሳይበር በላከው መግለጫ አስታውቋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top