ዩኒቨርሲቲው ለሁለት መምህራኑ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

1 Yr Ago 280
ዩኒቨርሲቲው ለሁለት መምህራኑ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ባደረገው ስብሰባ ለሁለት የዩኒቨርሲቲው መምህራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሰጥ ወሰነ።
የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ገምግሞ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት የአስተዳዳር ቦርዱ ለዶክተር ነጋ አሰፋና ለዶክተር ገላና አመንቴ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡
ዶክተር ነጋ አሰፋ በእናቶችና ህፃናት ጤና፤ ዶክተር ገላና አመንቴ ደግሞ በፊዚክስ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ፕሮፌሰር ነጋ አሰፋ ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ የመጀመሪያው ሙሉ ፕሮፌሰር መሆናቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top