የመዲናዋ አስተዳደር ለቦረና ህዝብ ያሰባሰበውን ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ ለኦሮሚያ ክልል መንግስት አስረከበ

9 Mons Ago
የመዲናዋ አስተዳደር ለቦረና ህዝብ ያሰባሰበውን ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ ለኦሮሚያ ክልል መንግስት አስረከበ
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቦረና ህዝብ ያሰባሰበውን ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የዓይነት እና የገንዘብ ድጋፍ ለኦሮሚያ ክልል መንግስት አስረክቧል።
የከተማዋ አስተዳደር በቀጣይም የክልሉ መንግስት ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ እየሰራቸው ያሉ ስራዎችን ሁሉ እንደሚደግፍ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ አረጋግጠዋል።
በተለያዩ ጊዜያት ከህዝብ ጎን በመቆም ለሚታወቁት የከተማዋ ባለሃብቶች፣ ድጋፉን ላስተባበሩ አመራሮች እና በድጋፉ ለተሳተፉ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ከንቲባዋ ምስጋና አቅርበዋል።
"ለቦረና ህዝብ ላሳያችሁት አለኝታነት እና ፍቅር ከልብ አመሰግናለሁ" ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top