በአማራ ክልል ለ4 ሺህ 401 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ

10 Mons Ago
በአማራ ክልል ለ4 ሺህ 401 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ
በአማራ ክልል ለ4 ሺህ 401 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን የክልሉ ፍትሕ ቢሮ አስታወቀ።
ለታራሚዎቹ ይቅርታ የተደረገው በይቅርታ ቦርዱ ተመርምሮ መስፈርቱን አሟልተው በመገኘታቸው እንደሆነም ተገልጿል።
በዚሁ መሠረት የክልሉ ምክር ቤት ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በክልሉ ፍትሕ ቢሮ አቅራቢነት በክልሉ ውስጥ በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ የሕግ ታራሚዎችን በይቅርታ እንዲፈቱ በወሰነው መሠረት መሆኑ ተገልጿል።
የይቅርታው ተጠቃሚ የሆኑት በይቅርታ አሰጣጥ መመሪያው ላይ የተገለጹ፣ የእስራት፣ የዕድሜ እና የጤና መስፈርቶችን ያሟሉ መሆኑን ከክልሉ ፍትሕ ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top