በከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራው የከንቲባዎች ቡድን ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት ከመጡ ከንቲባዎች ጋር የልምድ ልውውጥ አደረገ

1 Yr Ago
በከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራው የከንቲባዎች ቡድን ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት ከመጡ ከንቲባዎች ጋር የልምድ ልውውጥ አደረገ
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤና የባህርዳር አዳማ ደሴ ከንቲባዎች በደቡብ አፍሪካ በመካሄድ ላይ ባለው በAfrican Mayoral Leadership Initiative (AMALI) City Leadership Forum ቆይታቸው ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ከመጡ ከንቲባዎች ጋር የልምድ ልውውጥ አካሂደዋል፡፡
በዚሁ የልምድ ልውውጥ ላይ የአፍሪካ ከተሞችና ከንቲባዎች ከህዝብ ፍላጎት በመነጨ ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን ታሳቢ ያደረጉ ረጅምና ትውልድ የሚሻገሩ ዘላቂ አሻራን እያሳረፉ መሄድ የለውጥ አዙሪትን የሚያፋጥኑ ትላልቅ ትልሞችም መተለም እንደሚጠበቅባቸውና ከተሞቻቸውን ለነዋሪዎቻቸው ምቹ በማድረግ ለውጥን እያስመዘገቡ ህዝባቸውን ማገልገል እንደሚጠበቅባቸው አውስተዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ተሞክሮ ቀርቧል።
የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዘዳንት ዶ/ር አኪኑሚ ኤ.አዴንስያ በመድረኩ ለአፍሪካ ከንቲባዎች ባደረጉት ንግግር፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ ከተሞችን ለነዋሪቻቸው ምቹ ለማድረግ እንዲያስችል፤ ቀጥታ ለከተሞች ብድር ወይንም ፈንድ ማቅረብ እንደሚጀምር በዚሁ ወቅት ማብሰራቸው ለከተሞች ትልቅ እድል መሆኑ እንደተገለጸ ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top