የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንትን ሹመት አጸደቀ

1 Yr Ago
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንትን ሹመት አጸደቀ
የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበለትን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንትን ሹመት አጽድቋል።
ምክር ቤቱ አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት ከበደን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አድርጎ በ3 ድምፀ-ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ሹመታቸውን አጽድቋል።
በተመሳሳይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ወይዘሮ አበባ እምቢአለን ሹመት በሙሉ ድምፅ ያፀደቀ ሲሆን፤ ተሿሚዎችም በጉባኤው ፊት ቀርበው ቃለ-መሐላ ፈፅመዋል።
የቀድሞ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊ እና ምክትል ፕሬዝዳንት ሰለሞን አረዳ በገዛ ፍቃዳቸው ከኃላፊነት መልቀቃቸውም ተገልጿል።
በወንድወሰን አፈወርቅ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top