እ.አ.አ ከ2020 ወዲህ ዓለማችን ካመነጨችው 42 ትሪሊዮን ዶላር አዲስ ሀብት 2/3ኛው የሚሆነው ከዓለማችን ህዝብ አንድ በመቶ በሚሆኑት ባለፀጎች እጅ መግባቱን ኦክስፋም የተራድኦ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት አስታወቋል።
እነዚህ ባለፀጎች ለተራድኦ ድርጅቶች የሚቆርጡት ይገንዘብ መጠን ማደግ እንዳለበትም ድርጅቱ በሪፖርቱ አሳስቧል፡፡
በስዊስዘርላንድ ዳቮስ የተጀመረውን የአለም ኢኮኖሚ ፎረም ምክንያት ባድረግ ኦክስፋም ባወጣው ሪፖርት እንደገለጸው 99 በመቶ የሆነው የዓለም ህዝብ ከሚያገኘው የገንዘብ መጠን እጥፍ የሚሆነው ያህል የተያዘው አንድ በመቶ በሚሆኑት ግለሰቦች እጅ ነው፡፡
እንደ ሪፖርቱ ገለፃ ቢሊዮነር ባለፀጎች በቀን እስከ 2.7 ቢሊየን ዶላር ገቢ የሚያገኙ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ወደ 1.7 ቢሊየን የሚሆኑ ላብአደሮች በአስከፊ የኑሮ ውድነት ውስጥ ይገኛሉ፡፡
በሌላ ቡኩል ከዓለም ባላሃብቶች ግማሾቹ የሚኖሩት የውርስ ግብር በማይከፈልባቸው ሀገራት እንደሚኖሩ ተመልክቷል፡፡
እንደ ኦክስፋም ሪፖርት የዓለም ቢሊየነሮች እና ሚሊየነሮች ከሀብታቸው 5 በመቶ ቢገብሩ በዓመት 1.7 ትርሊዮን ዶላር ሀብት በመሰብሰብ ሁለት ቢሊዮን ህዝብ ከድህነት ማውጣትይቻላል፡፡
የኦክስፋም ዋና ዳይሬክተር ገብርኤል ቡቸር ለአልጀዚራ እንደገለፁት ሪፖርቱ በጣም አስደንጋጭ ብለውታል፡፡
“ዓለማችን ብዙ ቀውስ እያስተናገደች ባለችበት ሰዓት ሀብት በዚህ መልኩ በጥቅቶች እጅ መከማቸት ተገቢ አይደለም፡፡”
ዳይሬክተሩ አክለውም ሀገራት አዳዲስ የግብር ስርዓት እና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል አሰራር ማበጀት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ እንደ ናየጄሪያ እና ህንድ የመሳሰሉ ሀገራት በዚህ ረገድ አመርቂ ውጤት ማስመዝገባቸውንም ጠቅሰዋል፡፡