ጥሩነሽ ዲባባ ከ4 ዓመታት በኋላ ወደ ሩጫ ውድድር ልትመለስ ነው

1 Yr Ago
ጥሩነሽ ዲባባ ከ4 ዓመታት በኋላ ወደ ሩጫ ውድድር ልትመለስ ነው
የ3 ጊዜ የኦሎምፒክ እና የ5 ጊዜ የዓለም ሻምፒዮና አሸናፊዋ አትሌት ጥሩነሸ ዲባባ ከ10 ቀናት በኋላ በሚካሄደው 22ኛው የሂውስተን ግማሽ ማራቶን ላይ በመሮጥ ዳግም ወደ ውድድር ልትመለስ ነው::
አትሌት ጥሩነሽ በግማሽ ማራቶን 66 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ የግሏ ፈጣን ሰዓት ያላት አትሌት ነች::
በሂውስተን ግማሽ ማራቶንም በርቀቱ 67 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ ያላት አሜሪካዊቷ፣ ኤምሊ ሲሰን እና 66 ደቂቃ ከ47 ሰከንድ ያላት ኢትዮጵያዊቷ ህይወት ገ/ኪዳን የጥሩነሽ ተፎካካሪዎች ናቸው::

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top