ኢትዮጵያን ማገልገል ትልቅ ክብር እና መታደል ነው፡- አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ

11 Mons Ago
ኢትዮጵያን ማገልገል ትልቅ ክብር እና መታደል ነው፡- አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ
ኢትዮጵያን ማገልገል ትልቅ ክብር እና መታደል ነው ሲሉ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ገለፁ።
"ኢትዮጵያን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ እንድወክል እድል ለሰጡኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ምስጋና አቀርባለሁ" ብለዋል።
አምባሳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክት "ከኢትዮጵያ ጋር በመልካሙም ጊዜ ቢሆን በአስቸጋሪ ወቅት በጋራ ለቆሙ ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል" ሲሉም ገልፀዋል።
የስራ ዘመን ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ አገራቸው ለተመለሱ አምባሳደሮች በተከናወነው የምስጋና መርሃግብር እውቅና ከተሰጣቸው ስመጥር ዲፕሎማቶች መካከል በተመድ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ይገኙበታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top