በአዲስ አበባ በቀን ከ280 ሺህ በላይ እንጀራ የሚያመርት ፋብሪካ ሊገነባ ነው

1 Yr Ago 473
በአዲስ አበባ በቀን ከ280 ሺህ በላይ እንጀራ የሚያመርት ፋብሪካ ሊገነባ ነው
በአዲስ አበባ በቀን ከ280 ሺህ በላይ እንጀራ የሚያመርት ፋብሪካ ሊገነባ ነው።
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አራብሳ አካባቢ የሚገነባው ፋብሪካ 1000 ምጣዶች ይኖሩታል።
300 የስራ ቀናትን በመውሰድ 86 ሚሊዮን እንጀራ ይመረታል ብለዋል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመሰረተ ድንጋይ ሲያስቀምጡ።
ፋብሪካው ከአዲስ አበባ መሀል ከተሞች በመልሶ ማልማት የተነሱና ከእርሻቸው የተፈናቀሉ ስራ አጥ እናቶችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ብለዋል ከንቲባዋ።
በአካባቢያችን ያለውን ፀጋ በመጠቀም ሰርተን ሌማታችንን ለመሙላት ሁሉም እጆች ጠንክረው ሊሰሩ ይገባል ሲሉም አክለዋል።
አንድ ብለን የጀመርነውን ፋብሪካ በማብዛት እናቶች በዘመናዊ መንገድ እንጀራ በማምረት ኤክስፖርት እንዲያደርጉም ጭምር እንሰራለን ብለዋል ከንቲባዋ።
ይህን የመጀመሪያ የተባለውን የእንጀራ ፋብሪካ ኦቪድ የተሰኘ ተቋራጭ ለግንባታው ከተገመተው 150 ሚሊዮን ብር ግማሹን በግሉ በመሸፈን በ3 ወራት ውስጥ እንደሚያጠናቅቅ ቃል ገብቷል።
በፋብሪካው ከ3500 እስከ 4000 ወገኖች የስራ እድል ያገኛሉ ተብሏል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top