ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ ታምርት ሁለተኛው ጉብኝታቸው በገላን ከተማ የሚገኘውን የሆራ ኢንዱስትሪ ተመልክተዋል።
የኢንዱስትሪ ዘመናዊ የቡና ማቀነባበሪያ፣ መቁያ እና ሲሚንቶ ማሸጊያ ማምረቻ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ኢንዱስትሪ ማሳዳግ ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ ትልቅ ሚና እንዳለው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ላይ ሁሉም ባለሀብቶች እና ባለድርሻ አካላት እንዲሳተፉም በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።