የፔሌ ሥርዓተ-ቀብር ብዙ ሺዎች በተገኙበት ተፈፅመ

2 Yrs Ago 439
የፔሌ ሥርዓተ-ቀብር ብዙ ሺዎች በተገኙበት ተፈፅመ
የብራዚላዊው ኮኮብ እግር ኳስ ተጫዋች ፔሌ ሥርዓተ-ቀብር ብዙ ሺዎች በተገኙበት ተፈፅሟል።
ብራዚል የእግር ኳስ ኮኮቧን፣ ፔሌን፣ በሙሉ ስሙ ኤዲሰን አራንቴስ ዶ ናሲሜንቶን እስከወዲያኛው ሸኝታለች።
የ3 ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ፔሌ ባለፈው ሳምንት በ82 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል።
የብራዚል መንግሥትም በብዙኃኑ ዘንድ የምንጊዜም የእግር ኳስ ኮኮብ የሚባለውን ፔሌን ኅልፈት ተከትሎ ለ3 ቀናት የቆየ ብሔራዊ ኀዘን አውጆ ነበር።
ብራዚላውያንም ኮኮባቸውን በሳንቶስ ክለብ ኡርባኖ ካልዴራ ስታዲየም ለአንድ ቀን አስከሬኑ አርፎ መሰናበት ችለዋል።
የፔሌን አስከሬን በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ከ230 ሺህ በላይ ሰዎች ተገኝተው መሰናበታቸውን የቀድሞ ክለቡ ሳንቶስ አስታውቋል።
ታላቁ የእግር ኳስ ኮኮብ ፔሌ አስክሬን ወደ ቀብሩ በተሸኘበት ወቅትም በርካታ ብራዚላውያን ክብሩን እያወደሱ ሸኝተውታል።
በመጨረሻም የታላቁ ሰው የቀብር ሥነ-ሥርዓት በፖርት ሲቲ የቀብር ቦታ በዓለም ላይ ትልቁ ተብሎ በተመዘገበው ባለ 10 ፎቅ የቅብር ቦታ እንዲያረፍ በማድረግ ተጠናቋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top