ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሴፕ ታይፕ ኤርዶኻን ጋር በስልክ ተወያዩ

11 Mons Ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሴፕ ታይፕ ኤርዶኻን ጋር በስልክ ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሴፕ ታይፕ ኤርዶኻን ጋር ቁልፍ በሆኑ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ በስልክ መወያየታቸውን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፣ “ቁልፍ በሆኑ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ከቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሴፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጋር በስልክ ተነጋግረናል” ብለዋል።
በኢትዮጵያ እና በቱርክ መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማሳደግ እና ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት መስማማታቸውንም ገልጸዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top