በአውሮፓዊያኑ 2022 ሞሮኮ፣ ሞሪሸስ እና ደቡብ አፍርካ በፈጠራ ዘርፍ ከአፍሪካ የተሻለ ደረጃ ላይ ተቀመጡ

1 Yr Ago
በአውሮፓዊያኑ 2022 ሞሮኮ፣ ሞሪሸስ እና ደቡብ አፍርካ በፈጠራ ዘርፍ ከአፍሪካ የተሻለ ደረጃ ላይ ተቀመጡ
በአውሮፓዊያኑ 2022 ሞሮኮ፣ ሞሪሸስ እና ደቡብ አፍርካ በፈጠራ ዘርፍ እድገት ከአፍሪካ የተሻለ ደረጃ ላይ መቀመጣቸው ዓለም አቀፉ የአዕምሯዊ ንብረት ድርጅት ይፋ አደረገ።
ድርጅቱ ለ15ኛ ጊዜ ባወጣው ዓለም አቀፍ የፈጠራ አመላካች ሪፖቱ ላይ (Global Innovation Index ) እንዳመለከተው በርካታ የአፍሪካ ሀገራት በተገባደደው የአውሮፓዊያን 2022 በቴክኖሎጂ ዘርፍ እምርታዊ ለውጥ አስመዝግበዋል።
ይህ እምርታዊ ለውጥ አገራቱን ካደጉት ሀገራት ጋር የሚያቀራርባቸውን ፈጠራ መር ምጣኔ ሀብታዊ እድገት ለመዘርጋት በር የሚከፍት እንደሆነ ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡
አለም አቀፉ የአዕምሯዊ ንብረት ድርጅት(WIPO) በሪፖርቱ እንዳመለከተው ሞሮኮ፣ቱኒዚያ፣ ኬኒያ፣ ታንዛኒያ እና ዚምባቢዌ ከመካከለኛ ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ምድብ ውስጥ ከሚገኙ ሀገራት ከተጠበቀው በላይ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ሀገራት ሲሆኑ፣ ሩዋንዳ፣ ማዳጋስካር፣ ሞዛምቢክ እና ቡሩንዲ ደግሞ በፈጠራ ዘርፍ ከዕድገት ደረጃቸው አንፃር ተመጣጣኝ እድገት ያስመዘገቡ ናቸው፡፡
ከፍተኛ-መካካለኛ የኢኮኖሚ ምድብ ደረጃ ላይ ካሉት የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ደቡብ አፍርካ ከተጠበቀው በላይ የላቀ አፋፃፀም ያስመዘገበች ሲሆን ሞሪሸስ ደግሞ ከኢኮኖሚ ምድቡ የተጠበቀችውን ያስመዘገበች ሀገር ሆናለች፡፡
በተመሳሳይ ከዝቅተኛ- መካከለኛ የኢኮኖሚ መደብ ውስጥ ያሉት ጋና እና ሴኔጋል በኢኮኖሚያቸው ደረጃ የተጠበቀውን የፈጠራ እድገትን ያስመዘገቡ ሲሆኑ፣ በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ቡርኪናፋሶ፣ቶጎ እና ኒጀር በተመሳሳይ በተጠበቀው ልክ በፈጠራ ስራዎች እድገት ያስመዘገቡ መሆናቸውን የዓለም አቀፉ አዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ድርጅት ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርቱ ማመልከቱን ኖርዝ አፍሪካ ፖስት ዘግቧል፡፡
የተቀሩት የአፍሪካ ሀገራት ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚያዊ ናይጄሪያ እና ቦትስዋናን ጨምሮ በፈጠራ ስራዎች ዝቅተኛ ደረጃ ያስመዘገቡ ናቸው፡፡
በአጠቃለይ አፍሪካ እንደ አህጉር እራሷ በፈጠራ ዘርፍ አሁንም በዓለም ዝቅተኛውን ደረጃ የያዘች አህጉር እደሆነች የዳሰሳ ጥናቱ ጠቅሷል፡፡
እንደ ዳሰሳ ጥናቱ ስዊዘርላንድ በዓለም ቀዳሚ የፈጠራ መፍለቂያ ስትሆን ፣ አሜሪካ ደግሞ በሁለተኛነት ተቀምጣለች። ቻይና ፣ጃፓን፣ፈረንሳይ፣ ጣሊያን እና ካናዳ እስከ 10ኛ ባለው ደረጃ ውስጥ አለመካተታቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top