ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ አስጀመሩ

1 Yr Ago
ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ አስጀመሩ
ሚኒስትር ዴኤታው ሀገር አቀፍ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻውን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በስርጢ ጤና ጣቢያ በመገኘት አስጀምረዋል።
ዶ/ር ደረጄ በዚሁ ወቅት በሚቀጥሉት አስር ቀናት 15.5 ሚሊዮን ህጻናት እንደሚከተቡ ገልፀዋል።
ህጻናት በታሰበው ልክ እንዲከተቡ ሁሉም አመራርና የህብረተሰብ ክፍል በትኩረት እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ በከተማዋ 520 ሺህ ህጻናትን ተደራሽ ለማድረግ መታሰቡን ገልፀዋል።
ከኩፍኝ ክትባቱ በተጓዳኝ በምግብ አለመመጣጠን የተጐዱትን የመለየት፣ የአንጀት ጥገኛ ትላትሎች የመከላከያ መድሃኒት የመስጠት፣ በፊስቱላ የተጐዱ እናቶች ልየታ እና ሕክምና እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በላይ ለሆኑ የኮቪድ 19 ክትባት የመስጠት ተግባራት እንደሚከናወኑ ተገልጿል።
በብሩክ ተስፋዬ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top