ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ የካፍ የቅድመ ማጣርያ ውድድር ያደርጋሉ

10/08/2022 01:20
ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ የካፍ የቅድመ ማጣርያ ውድድር ያደርጋሉ

በአፍሪካ የክለቦች ውድድር መድረክ ኢትዮጵያን የሚወክሉት ሁለት ክለቦች ተጋጣሚያቸውን አውቀዋል። ትላንት ምሽት በወጣው ድልድል የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ቅዱስ ጊዮርጊስ በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ከ ሱዳኑ አል ሂላል ኦምዱርማን ይገጥማል። ካይሮ ላይ በወጣው የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ እጣ አወጣጥ ፕሮግራም መሠረት ፈረሰኞቹ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በሜዳቸው ያደርጋሉ። ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው ፋሲል ከነማ ደግሞ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከቡሩንዲው ቡማሙሩ ክለብ ጋር ለመጫወት ተመድቧል።

ግብረመልስ
Top