በኮሎምቢያ ካሊ በተካሄደው ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ12 ሜዳልያ በ3ኛነት አጠናቀቀች

1 Yr Ago
በኮሎምቢያ ካሊ በተካሄደው  ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ12 ሜዳልያ በ3ኛነት አጠናቀቀች
በኮሎምቢያ ካሊ ላለፉት 6 ቀናት በተካሄደው ከ20 ዓመት በታች የወጣቶች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ12 ሜዳሊያ ሶስተኛ ደረጃን አጠናቅቃለች፡፡ የአትሌቲክስ ቡድኑ በቆይታው በ6 ወርቅ፣ በ5 ብር እና 1 የነሃስ በድምሩ በ12 ሜዳልያዎችን በማምጣት ኢትዮጵያ ከዓለም አሜሪካን እና ጃማይካን ተከትላ በ3ኛነት ፣ከአፍሪካ ደግሞ በ1ኛነት እንድታጠናቅቅ አስችሏል፡፡ በሻምፒዮናው 19 አትሌቶች በሁለቱም ፆታ በ10 የውድድር ተግባራት ማሰለፉን ያስተወቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፣የተገኘው ውጤት እስከ ዛሬ ከተካሄዱት የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳትፎ ታሪክ ከፍተኛው መሆኑን አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከተሳተፈችበት ውስን የውድድር ተግባራት አንፃር የተገኘው ውጤት እጅግ የሚያኮራ መሆኑንም ፌደሬሽኑ ገልጿል። ኬንያ 3 ወርቅን ጨምሮ በአጠቃላይ በ10 ሜዳልያ ኢትዮጵያን ተከትላ ከዓለም 4ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡ አሜሪካ በቀዳሚነት የጨረሰችው 7 የወርቅ፣4 የብርና 4 የነሀስ በድምሩ በ15 ሜዳልያ ሲሆን፣ጃማይካ ደግሞ በ6 ወርቅ፣7 ብር እና 3 ነሃስ በድምሩ በ16 ሜዳልያ በ2ኛነት አጠናቃለች፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top