ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ

04/08/2022 08:04
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፣ “የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ስብሰባችንን አካሂደናል፤ ባለፈው ዓመት የሚያበረታታ የወጪ ንግድ አፈጻጸም፣ ቀጥተኛ የውጭ ሙዓለ ነዋይ ፍሰት መጨመር ታይቷል።” ብለዋል።
ባለፉት ሁለት ወራት የዋጋ ግሽበት መቀነስ፣ ከፍተኛ የአረንጓዴ ዐሻራ ክንውን፣ የበጎ ፈቃደኝነት ተግባራት፣ የሬሚታንስ ጭማሪ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥራ ክንውን የተመዘገቡበት እንደ ሆነ ኮሚቴው ማረጋገጡንም ጠቁመዋል። በዚህ ዓመት የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ መቀጠል በእጅጉ አስፈላጊ እንደሆነ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመልእክታቸው ያሰፈሩት።
 
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
ግብረመልስ
Top