የክልሉ መንግሥት ከውስጥ በአንድነት የጠነከረ ክልል እና ሀገር እንዲገነባ እየሠራ ነው”፦ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

1 Yr Ago
የክልሉ መንግሥት ከውስጥ በአንድነት የጠነከረ ክልል እና ሀገር እንዲገነባ እየሠራ ነው”፦ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ
የአማራ ክልል መንግሥት ከውስጥ በአንድነት የጠነከረ ክልል እና ሀገር እንዲገነባ እየሠራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ። የወልዲያ ከተማ ወደ ሪጂዮፖሊታን ከተማነት ደረጃ ማደጓን ተከትሎ የምስጋና መርሐ-ግብር በወልዲያ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመርሐ-ግብሩ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ እና ብልፅግና ፓርቲ አማራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሽጥላን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከወልድያ ከተማ ሕዝብ ጋር ታድመውበታል። የወልዲያ ከተማ ለ5 ወራት በአሸባሪው ህወሓት ቁጥጥር ሥር ሆና በርካታ ግፍ ያስተናገደች ከተማ ናት። የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋሁን ባንተአብል በመርሐ-ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልእክት፣ ዞኑ በወረራው ከደረሰበት ጉዳት አገግሞ ወደ ቀድሞ ሁኔታው እንዲመለስ እና ወልዲያ ከተማም የሚገባትን የከተማ ዕድገት እንድታገኝ ለተደረገው ጥረት የክልሉን መንግሥት አመስግነዋል። ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በበኩላቸው፣ ሰሜን ወሎ በጠላት ወረራ ጉዳት የደረሰበት ቢሆንም ተጎድተን እና ተዳክመን እንደማንቀር ያረጋገጡ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል። ከድል መልስ ከደረሰው ስብራት ፈጥኖ በማገገም የወደመውን ሀብት እና የተቋማት አገልግሎት ዳግም ለመመለስ የተደረገው ጥረት አመርቂ ነው ሲሉም አክለዋል። በተለይም የመንግሥት ተቋማት ከደረሰባቸው ጉዳት አንፃር የመንግሥት ሠራተኞች አገልግሎት ለማቅረብ ያለመቀመጫ ወንበር እና ቁሳቁስ በትጋት መንግሥት እና ሀገር ስለመቀጠሉ ማረጋገጫ በመሆናችሁ እናመሠግናለን ብለዋል። በመሆኑም በሕዝብ እና አመራሩ ቁርጠኝነት ወልዲያ ወደ ቀድሞ ክብሯ እና ድምቀቷ በመመለሷ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ። በዚህ ችግር ውስጥ እና አሸባሪው ድል ከሆነ በኋላ በዞኑ በ2014 በጀት ዓመት በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሁኖ የተሻለ አፈፃፀም ለፈፀሙ ተቋማት እና ግለሰቦች እውቅና እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top