ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ተወያዩ

27/07/2022 12:59
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ተወያዩ
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ተወያይተዋል። በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቀባበል አድርገውላቸዋል። በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ መንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት እያደረጉ ይገኛል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በግብጽ፣ በኮንጎ ብራዛቪልና በኡጋንዳ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።
ግብረመልስ
Top