አቶ ደመቀ መኮንን ከሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ተወያዩ

27/07/2022 12:56
አቶ ደመቀ መኮንን ከሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ተወያዩ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ከሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር በፅ/ቤታቸው ተገናኝተው ተወያዩ። ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ትላንት ምሽት አዲስ አበባ የገቡት የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ከውይይቱ በኋላም የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫውም፣ በሩሲያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተዳሰዋል።
ግብረመልስ
Top