በጅቡቲ የነዳጅ ማከማቻ ለመገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

05/05/2022 01:13
በጅቡቲ የነዳጅ ማከማቻ ለመገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና የጅቡቲው ግሬት ሆርን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ በጅቡቲ የነዳጅ ማከማቻ ለመገንባት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
በጅቡቲ ዳመርጆግ ኢንዱስትሪ ፓርክ እንዲገነባ የተታሰበው ማከማቻው በአካባቢው እያየለ የመጣውን የነዳጅ ምርት ፍላጎት የሚያሟላ መሆኑ ተግልጿል፡፡
ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ማሞ ምህረቱ እና የግሬት ሆርን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ሊቀ መንበር አቡበከር ኦማር ሃዲ ፈርመዋል፡፡
ስምምነቱ የኢትዮያን ወሳኝ ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች ለመፍታት እና መጪው ትውልድ የተሻለ የኑሮ ደረጃ እንዲኖረው ታቀዶ ከሚሰሩ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች መካከል መሆኑን አቶ ማሞ ገልፀዋል፡፡
የነዳጅ ምርቶች ኢትዮጵያ ከውጭ ከምታስገባው ምርት ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚወስድ የተጠቀሰ ሲሆን፤ በቀጣይ አስር አመታት ውስጥም ፍላጎቱ በእጥፍ ያድጋል ተብሏል፡፡
ሆኖም ከፍተኛ አቅም ያለው ዘመናዊ ማከማቻ አለመኖሩ ለዚህ ዕድገት እንቅፋት መሆኑም ተነስቷል።
ምርቱ ለኢትዮጵያ እና ለሌሎች ተጠቃሚዎች በአስተማማኝ ሁኔታ ጊዜውን ጠብቆ እንዲደርስ የሚያስችል ወጪ ቆጣቢ መፍትሄ እመንደሚያስፈልግም ተገልጿል፡፡
አዲሱ የነዳጅ ማከማቻም እያደገ የመጣውን የአካባቢውን የምርት ፍላጎት የሚያሟላ እና ለባለ አክሲዮኖቹም ከፍተኛ ገቢን እንደሚያስገኝ ከጅቡቲ የወደብ እና ነፃ ቀጠና ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
ግብረመልስ
Top