የሱዳን የቀድሞ ፕሬዝደንት አልበሽር ሆስፒታል ውስጥ ሆነው የሚያሳይ ቪዲዮ መወጣት ቁጣን ቀሰቀሱ

1 Yr Ago
የሱዳን የቀድሞ ፕሬዝደንት አልበሽር ሆስፒታል ውስጥ ሆነው የሚያሳይ ቪዲዮ መወጣት ቁጣን ቀሰቀሱ

ሱዳናውያን በሆስፒታል ውስጥ ለፕሬዝዳንቱ የተሰጠው እንክብካቤ አበሳጭቷቸዋል

በህዝባዊ አመጽ ከስልጣን የተነሱት የቀድሞ የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በጠና ታመው በሆስቲታል ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል(ቪዲዮ) መውጣቱ በበርካታ ሱዳናውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ወደ ሆስፒታል የተወሰዱት በእርቤት ሳሉ በመታመማቸው ነው፡

በሱዳን በፈረንጆቹ 1989 የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት በመምራት ወደ ስልጣን በመምጣት እና በሙስና ክስ ምክንያት በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከሶስት አመት በፊት ከስልጣን የተነሱት በሽር ለእስር ተዳርገዋል፡፡

ሮይተርስ የተንቀሳቃሽ ምስሉን ምንጭ እና እውነተኛነት ማረጋገጥ እንደማይችል በዘገባው ጠቅሷል፡፡ ነገርግን የፕሬዝደንቱ ጠበቃ ፕሬዝደንት በሽር በእስር ላይ መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡

በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ ፕሬዝደንቱ በሆስፒታል ክፍላቸው ውስጥ ሆነው ሊጠይቋቸው የመጡትን ሰዎች ሰላም ሲሉ፣ የተለመደ ልብስ ለብሰው እና ሰአት አድርገው በሆስፒታሉ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ ብሏል ዘገባው፡፡

ይህ ተንቀሳቃሽ ምስል ከፍርድ ቤት ውጭ የታየ የመጀመሪያው ተንቀሳቃሽ ምስል ነው ተብሏል፡፡ በሌላ ተንቀሳቃሽ ምስል ደግሞ ፕሬዝደንቱ ሌሎች በሆስፒታሉ ያሉ ታማማሚዎች ሲጠይቁ ታይተዋል፡፡

የፕሬዝዳንቱ ጠበቃ አብዱልራህማን አል ከሊፋ ፕሬዝደንቱ ወደ ሆስፒታል የተወሰዱት በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የተወሰኑ ሱዳናውያን ፕሬዝደንቱ እንዲድኑ ሲለምኑ፣ሌሎች ለፕሬዝደንቱ በተደረገው እንክብካቤ ቁጣቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ አንድ የማህራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ይህን ለፕሬዝዳንቱ ተደረገ ያለውን እንክብካቤ ካየ በኋላ የአብዮቱ ሰማእታት ሞት ትርጉም የለውም ሲል ብስጭቱን ገልጿል፡፡

ሱዳን አሁን ላይ አልበሽርን ከስልጣን ባነሱት የጦር ጀነራሎች እየተዳደረች ትገኛለች፡፡ በሱዳን ስልጣን የያዙት ጀነራሎች ስልጣናቸውን ወደ ሲቪል አስተዳደር እንዲቀይሩ የሚፈልጉ ተቃውሞውች ሱዳን እስካሁን ድረስ እንዳትረጋጋ አድርገዋታል፡፡

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top