“በይቻላል መንፈስ ከተጫወትን ካሜሩንን እናሸንፋለን”- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች

13/01/2022 10:23
“በይቻላል መንፈስ ከተጫወትን ካሜሩንን እናሸንፋለን”- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች

 “በይቻላል መንፈስ ከተጫወትን ካሜሩንን እናሸንፋለን”- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች

***********************************

በይቻላል መንፈስ ከተጫወትን ካሜሮንን እናሸንፋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ተናገሩ።

ቡድኑን ለመደገፍ ካሜሩን የሚገኙት ደጋፊዎች ኢትዮጵያን በበጎ መልኩ እያስጠሩ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

በዛሬው ጨዋታም ያላቋረጠ ድጋፍ እንደሚያደርጉም በስፍራዉ ለሚገኘው የኢቢሲ ሪፖርተር ተናግረዋል።

የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች በዛሬው እለት የሚደረጉ ሲሆን ካሜሩን             ከኢትዮጵያ አንድ ሰዓት ላይ የሚካሄድ ሲሆን ኬፕቨርድ ከቡርኪናፋሶ ምሽት አራት ሰዓት ላይ የሚገናኙ ይሆናል።

ምድብ አንድን ካሜሩን እና ኬፐቨርድ በተመሳሳይ ሶስት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ምድቡን ሲመሩ ቡርኪናፋሶ እና ኢትዮጵያ በዜሮ ነጥብ ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃን ከምድባቸው ይዘዋል።

ሀብታሙ ካሴ (ከካሜሩን)

ግብረመልስ
Top