ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ አዲስ አበባ ገባች

2 Yrs Ago
ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ አዲስ አበባ ገባች
 
በ#NoMore ዘመቻ የኢትዮጵያን እውነታ ለዓለም ያሳወቀችው ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ አዲስ አበባ ገብታለች።
ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትደርስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች እንግዶች አቀባበል አድርገውላታል።
ጋዜጠኛዋ ኑሮዋን በአሜሪካ አድርጋ በኢትዮጵያ ላይ ሲደረግ የነበረውን ኢ-ፍትሐዊ አካሄድ ስትቃወም መቆየቷ ይታወቃል።
ጋዜጠኛ ሄርሜላ ወደ ሀገር እንደገባች በሰጠችው አስተያየት “ለሀገር መሥራት የሚገባን ብዙ በመሆኑ ይበልጥ መበርታት አለብን” ብላለች።
ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም ደረጃ በንቅናቄ መልክ እየተካሄደ ባለው የ#NoMore (#በቃ) በመሳተፍ ለሀገሯ ሚና በመጫወቷ ደስተኛ መሆኗንም ተናግራለች።
ገና ብዙ የሚሠሩ ነገሮች በመኖራቸው በቀጣይም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በትጋት በመሳተፍ ለሀገሩ የአቅሙን ሚና መጫወት እንዳለበት ጥሪ አስተላልፋለች።
“ሀገሬ በመገኘቴ ደስተኛ ነኝ፤ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ በተደረገላት አቀባበል አስደስቶኛል፤ አመሰግናለሁ” ብላለች ጋዜጠኛ ሄርሜላ።
ሔርሜላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡትን ጥሪ ተቀብለው እየመጡ ከሚገኙ የዲያስፖራዎች መካከል ናት።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top