ከተከፈቱ ሕገ-ወጥ የገንዘብ መላኪያ ድረ-ገፆች ተጠንቀቁ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

2 Yrs Ago
ከተከፈቱ ሕገ-ወጥ የገንዘብ መላኪያ ድረ-ገፆች ተጠንቀቁ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የተሻለ የመዘርዘሪያ እና የመላኪያ ዋጋ እናቀርባለን በማለት አንዳንድ አጭበርባሪዎች መተግበሪያዎችን እየሠሩ ድረ-ገፅ ላይ እየለቀቁ በመሆኑ ሰዎች እንዲጠነቀቁ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሳሰበ።
 
በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ባለው ጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚላክን ገንዘብ ሕጋዊ ለማድረግ እና የተበታተነ የገንዘብ አላላክን በአንድ ቋት ለመድረግ እንዲቻል http://xn--www-86o.eyezonethiopia.com/ አማካኝነት በማሰባሰብ ላይ እንደሆነ ይታወቃል።
 
ሆኖም አንዳንድ አጭበርባሪዎች ‘የተሻለ የመዘርዘሪያ እና የመላኪያ ዋጋ እናቀርባለን’ በማለት መተግበሪያዎችን እየሠሩ ድረ-ገፅ ላይ እየለቀቁ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ባንኩ አሳስቧል።
 
እንዲህ ዓይነቱ የማጭበርበር ሥራ ዳያስፖራው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚያደርገውን ድጋፍ ለማስተጓጎል እና ለአገር የሚጠቅመውን የውጭ ምንዛሬ ወደራሳቸው አገር በማስቀረትና ህጋዊ ያልሆነ የገንዘብ ዝውውርን አገር ውስጥ በማስፋፋት አገርን የሚጎዳ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን መገንዘቡን ባንኩ ገልጿል።
 
 
እነዚህ አካላት በተለይ በቅርቡ ወደ አገራቸው የሚመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ኢላማ አድርገው እየተንቀሳቀሱ ነው ያለው ባንኩ፥ ህጋዊ ያልሆኑ የገንዘብ አዘዋዋሪ ተቋማትን ባለመጠቀም ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን እንዲከላከሉ ባንኩ መልዕክቱን አስተላልፏል።
 
ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ከ5 ዶላር ጀምሮ http://xn--eyezonethiopia-py1d.com/ ድረ-ገጽን በመጠቀም ድጋፋችውን እንዲያደርጉ ባንኩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ ጠይቋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top