የጀርመን መንግስት ለኢትዮጵያ የ120 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማዘጋጀቱን አስታወቀ

4 Yrs Ago
የጀርመን መንግስት ለኢትዮጵያ የ120 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማዘጋጀቱን አስታወቀ

የጀርመን መንግስት የኮቪድ-19 መከላከል የሚውል ለኢትዮጵያ የ120 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ብሪታ የጀርመን መንግስት ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ፣ ትምህርት፣ ጤና እና የጨርቃጨርቅ ዘርፍ ሰራተኞችን ለመደገፍ የሚያስችል የ120 ሚሊየን ዩሮ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም ለከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የኮቪድ-19 መከላከል የሚውሉ የቁሳቁስ ድጋፎችን ከጀርመን አምባሳደር ብሪታ ቫግነር ዛሬ ተረክበዋል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ ፕሮፌሰር ሂሩት እንዳሉት የጀርመን መንግስት የኮቪድ 19 ወረርሽን ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ የሚያስችሉ ኢንፍራሬድ ቴርሞሜትሮችን፣ የእጅ መታጠቢያ ሳሙናዎችን የዋይፋይ ዶንግል እና በእግር ውሃ በማፍሰስ እጅ መታጠብ የሚቻልበት ማሽን ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ይሄንንም ለከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በማከፋፈል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚሰሩትን ስራ እንዲያግዝና በተለይ ሰራተኞች ከቤት ሆነው እንዲሰሩ እንደሚረዳ ጠቁመዋል፡፡

በጀርመኑ ጂአይዜድ በኩል የቴክኖሎጂ ሽግግር ፕሮጀክት በመንደፍ ኮተቤ በሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት የተመረቱ በእግር በመረገጥ ውሃ የሚያፈስሱና እጅን ለመታጠብ የሚስችሉ ማሽኖችን ድጋፍ አድርጎ 600 ያህል በማስመረት ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርትና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማትና ቢሮዎች በማዳረስ ቴክኖሎጂውን አባዝተው ለአከባቢያቸው ማህበረሰብ ጥቅም እንዲያውሉ ለማድረግ እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top