በ17 ዓመቱ 5 ዋንጫዎችን ያገኘው የእግር ኳሱ ክስተት

17 Days Ago 290
በ17 ዓመቱ 5 ዋንጫዎችን ያገኘው የእግር ኳሱ ክስተት

የእግር ኳሱ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በሰለጠነበት ላሜሲያ አካዳሚ ሰልጥኖ ሜሲን እያደነቀና አርአያ አድርጎ ወደ ኳስ ህይወት የገባው ላሚን ያማል አሁን የዘመኑ ኮከብ  ለመሆን ጉዞውን ጀምሯል።

ላሚን ያማል ባርሴሎና ትላንት ማታ እስፓኞልን 2 ለ 0 አሸንፎ የላሊጋውን ዋንጫ ለ28ኛ ጊዜ ሲያሸንፍ ቀዳሚዋን ግብ አስቆጥሯል። ኳስ አመቻችቶ በማቀበል ሁለተኛዋ ግብ እንድትቆጠርም ምክንያት ሆኗል። 

ክርስታያኖ ሮናልዶ በማድሪድ ሁለት የላሊጋ ዋንጫዎችን ለማሸነፍ የፈጀበትን 9 ዓመታት ያማል በ2 ዓመታት ውስጥ ማሳከት ችሏል።

በውድድር ዓመቱ ባደረጋቸው 45 ጨዋታዎች 17 ግቦችን አስቆጥሯል፤ 25 ለግብ የሚሆን ኳሶችን አቀብሏል።

አዲሱ የእግር ኳስ ኮከብ ያማል ዘንድሮ ባርሴሎና 3 ዋንጫዎችን እንዲያሸንፍ ወሳኝ ሚና ከነበራቸው ተጫዋቾች መካከል ግንባር ቀደሙ ነዉ።

በ2024/25 የውድድር ዓመት የላሊጋውን፣ የኮፓ ዴላሬይ እና ሱፐር ካፕ ዋንጫዎችን በማሸነፍ በውድድር ዓመቱ የሶስትዮሽ ድል አድርጓል።

የስፔን ብሔራዊ ቡድን የ2024 የአውሮፓ ዋንጫን ሲያሸንፍ የቡድኑ የጀርባ አጥንት ነበር።

በዓለም እግር ታሪክ በ17 ዓመቱ 5 ዋንጫዎችን በማሸነፍ መጀመሪያው እንደሆነ እየተነገረ ይገኛል።

በ17 ዓመት እድሜው 2 የላሊጋ ዋንጫ፣ 1 የኮፓ ዴላሬይ ዋንጫ፣ 1 የስፔን ሱፐር ካፕ ዋንጫ እና 1 የአውሮፓ ዋንጫዎችን አሸንፏል።

አዳጊው በግሉ በርካታ ሽልማቶሸችን ያገኘ ሲሆን ከእነዚህ መካከልም፡-

ጎልደን ቦይ አሸናፊ-በአውሮፓ ምርጥ ተጫዋች (በ2024)፣

የላሊጋው ኮከብ ወጣት ተጫዋች (በ2024)፣

ራይሞንድ ኮፓ ሽልማት አሸናፊ - በዓለም ከ21 ዓመት በታች ኮከብ ተጫዋች (2024)፣

የዓለም ምርጥ ወጣት ተጫዋች (በ2024)፣

በዓለም ኮከብ ወጣት ተጫዋች (በ2023)፣

የአውሮፓ ኮከብ አዳጊ ተጫዋች (በ2024)፣

የላውረስ የዓመቱ ክስተት ተጫዋች (በ2025)፣

የዓለም ምርጥ ብሔራዊ ቡድን፣ የአውሮፓ ምርጥ ቡድን፣ የአለም ምርጥ ወጣት ቡድን አባል (ከስፔን በ2024) ተጠቃሽ ናቸው።

ሜሲ በሰለጠነበት ሰልጥኖ ሜሲን መተካት የቻለው ላሚን ያማል አሁን በስፔን ብቻ ሳይሆን በዓለም እግር ኳስ አዲስ ክስተት መሆን ችሏል።

ባሎንዶር ሽልማት ሊያሸንፍ ይችላል እየተባለም ይገኛል።

በላሉ ኢታላ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top